Internet Banking
Internet Banking

ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለመምረጥ የእጩ ተወዳዳሪዎችን ጥቆማ ከሰኔ 4 ቀን 2ዐ15 እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ ይቀበላል፡፡

በመሆኑም፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንካችን እድገትና መሻሻል የላቀ ውጤት ለማበርከት ብቃቱ ያላቸውንና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን በማክበር እናቀርባለን፡፡

ለጥቆማው የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች ሰኔ 4 በአዲስ ዘመን፤ ሰኔ 4፣ ሐምሌ 2፣ ነሐሴ 7 እና 14 በሪፖርተር እንዲሁም ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ እትም መመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs