Internet Banking
Internet Banking

ባንካችን በአጋርነት የተሳተፈባቸው የጉራጌ ልማትና ባሕል ማህበር የችግኝ ተከላ እና የኬሮድ የ15 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሔደ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለሁለቱም ሁነቶች አጋር በመሆን ማህበራዊ ሀላፊነቱን ተወጥቷል።

የባንካችን የሥራ ሀላፊዎችም በጉራጌ ዞን በእኖር፣ ኤነር መገር ወረዳ እና በወልቂጤ ከተማ በተካሔዱት በእነዚህ መርሐ-ግብሮች በመገኘት ተሳትፈዋል።

ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው 12ኛው ዙር የጉራጌ ልማትና ባሕል ማህበር የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ በርካታ እንግዶች የተገኙ ሰሆን በእለቱ 20,000(ሃያ ሺህ) ችግኞች ተተክለዋል።

በ4ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫም ዛሬ ማለዳውን በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተካሔደው የኬሮድ ሩጫም አትሌት ኮማንደር ሰለሞን ባረጋና አትሌት ሙክታር ኢድሪስን ጨምሮ የዘርፉ ታላላቅ ሰዎች ተገኝተዋል።

ባንካችንም መርሐ-ግብሮቹን በማድመቅ የተለያዩ የገፅታ ግንባታ ሥራዎችን አከናውኗል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

ሁነቶቹን በከፊል የሚያሳዩ ምስሎችን በዚህ ማስፈንጠሪያ https://www.nibbanksc.com/gallery/ መመልከት ይችላሉ፡፡

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs