Internet Banking
Internet Banking

ንብ ባንክ ከአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ጋር ለመሥራት ተፈራረመ::

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር በጋራ ለመሥራት (የስትራቴጂክ አጋርነት) የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ፡፡

የሥምምነት ፊርማው በባሕር ዳር ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ልዑልሰገድ ንጉሤ  እና የአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ.ሮ ትቅደም ወርቁ መፈረማቸውን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በአማራ ክልል ተደራሽ ለመሆን እየሠራ ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ እንዲቻል በውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ የዲስትሪክት ቢሮና በርካታ ቅርንጫፎች በክልሉ ከፍቶ  በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ለዜጎች ተስፋ መሆን ከመቻሉ በተጨማሪ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል በመፍጠር ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

የአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር በ1980 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 151,106 ንቁ አባላት፣ 32 የገንዘብና ቁጠባ ማኅበራት፣ በ102 ከተሞች ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ106 አገር በቀል እና ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ማኅበሩ በጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ እና ደሴ ከተሞች መሥሪያ ቤቶች ያሉት ሲሆን 151,106 ንቁ አባላት፣ በክልሉ ከ357,000 እስከ 422,000 ነጋዴዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 51 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ከማኅበሩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ÷ በአሁኑ ወቅት ከአራት መቶ በላይ ቅርንጫፎች፣ ከሰባት ሺህ በላይ ሠራተኞች እንዲሁም እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 2022 ከሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ ሀብትም ከ61.2 ቢሊዮን ባላይ የደረሰ ሲሆን በቀጣይም አገልግሎቱን የበለጠ ዘመናዊ በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋት ጠንክሮ እንደሚሠራ ባንኩ አስታውቋል፡፡

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs