Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከግብር በፊት 2 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ።

ባንኩ 24ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አከናውኗል።

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ወልደትንሣይ ወ/ጊዮርጊስ የባንኩን አመታዊ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፤ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ከብር 77 ቢሊዮን በላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ወይም የ25 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት ያልተጣራ 2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም ነው የቦርድ ሊቀመንበሩ በሪፖርቱ የተናገሩት።

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የአጠቃላይ የብድር መጠን ከብር 54 ቢሊዮን መብለጡን የጠቆሙት አቶ ወልደትንሣይ፤ ይህም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲተያይ የ14 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

ባንኩ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በማከናወንም ጠቅላላ ጉባዔውን አጠናቋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs