Internet Banking
Internet Banking

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ በይፋ ስራ ጀመሩ።

በቅርቡ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሹመታቸውን የተቀበሉት አቶ ሄኖክ ከበደ ወደ ቢሯቸው ሲገቡ በባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድና በማኔጅመንት አባላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

 

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ”የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ እምነት ጥሎብኝ ለዚህ ሃላፊነት ስላጨኝ፤ ደግሞም ስለመረጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ” ብለዋል።

 

”የንብ ባንክን ማሕበረሰብ በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ” ያሉት አቶ ሄኖክ ”በተጣለብኝ እምነት መሰረት ባንኩን ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ወደሚገባው ላቅ ያለ ቦታ ለማድረስ ዝግጁ ነኝ” ብለዋል።

 

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ በበኩላቸው አዲሱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመላው የባንኩ ማሕበረሰብ ስም ”እንኳን ደህና መጡ” በማለት መልካም የሥራ ጊዜ የተመኙ ሲሆን ”አቶ ሄኖክ በእውቀትም ሆነ በተግባር የተፈተነና ለባንካችንም ትክክለኛና ተገቢ ሰው ነው” ብለዋል።

 

”ታታሪው የንብ ሰራዊትን እየመሩም ባንኩን ለተሻለ ደረጃ እንደሚያበቁ እምነቴ ፅኑ ነው” ብለዋል።

 

በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉት አቶ ሄኖክ ከበደ በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ለሰባት ዓመት ደግሞ የዲስትሪክት ማኔጀር ሆነው ሰርተዋል፡፡

 

በተጨማሪም በዳሽን ባንክ ከስድስት ዓመት በላይ የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር እንዲሁም በአማራ ባንክ ለ2 (ሁለት) ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት አገልግለዋል፡፡

 

አቶ ሄኖክ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ ለሌላ ሐገራዊ ተልዕኮ ተመርጠው በቅርቡ ባንኩን በይፋ መሰናበታቸውን ተከትሎ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ወደ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የመጡት።

 

መልካም የሥራ ጊዜ!
****
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

You May Also like

Reports

Jobs