ደንበኞች በቀላሉ ባንኩን በሚመለከት መረጃ ማግኘት የሚችሉበት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የጥሪ መቀበያ ማዕከል (Call Center) 9698 ሥራ ጀመረ፡፡
የባንኩ ደንበኞችና ተገልጋዮች ባንኩን በሚመለከት ለሚፈልጉት ማንኛውም የአገልግሎት ጥያቄና መረጃ ከክፍያ ነጻ 9698 በመደወል ምላሽ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ከባንኩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
ተገልጋዮችና ደንበኞች እንግልት ሳይገጥማቸው ባሉበት ሆነው በመደወል የተሟላ መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡