የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎችን ሹመት ማጽደቁን አስታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት፤ አቶ ሰይፉ አገንዳ ኬርጋ – ቺፍ የከስተመርና ኦፕሬሽን ኦፊሰር፣ አቶ ሰለሞን ጎሽሜ በጅጋ – ቺፍ የኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር፣ አቶ መልካሙ ሰለሞን ይመር – ምክትል ፕሬዚዳንት ሂዩማን ካፒታል፣ አቶ አብርሃም ተስፋዬ አበበ – ምክትል ፕሬዚዳንት የስትራቴጂና ማርኬቲንግ እና አቶ አሚነ ታደሰ ተስፉ – ምክትል ፕሬዚዳንት የኢንተርናሽናል ባንክ ኦፕሬሽን ሆነው ተሹመዋል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ሹመቱን ማጽደቁን ባሳወቀበት ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው፤ በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2000፣ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1159/2011 እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/79/2021 አንጻር የተላኩለትን ሰነዶች እና ሌሎች ማስረጃዎች ላይ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በቅርቡ የስትራቴጂክ (መሪ) እቅድ ክለሳ ያደረገ ሲሆን፤ ይኸው የከፍተኛ ኃላፊዎች ሹመትም ከዚሁ ክለሳ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀውን አዲስ የባንኩን አደረጃጀት መሠረት ያደረገ ነው፡፡
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!