Internet Banking
Internet Banking

ባንካችን አጋር የሆነው ኬሮድ የልማት እና ስፖርት ማህበር ለ4ኛ ጊዜ ለሚያከናውነው የጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ኬሮድ ሐምሌ 14 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚያከናውነውን የጎዳና ላይ ሩጫ አስመልክቶ በባንካችን ዋና መሥሪያ ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ ላለፉት 3 አመታት የኬሮድ ሩጫን ሲደግፍ የቆየው ንብ ባንክ ዘንድሮም አጋርነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች አንዱ የሆነው የስፖርቱን ዘርፍ ከመደገፍ ባለፈ በበርካታ ሀገራዊ ማህበራዊ ጉዳዮችም የራሱን ድርሻ እየተወጣ የመጣ ባንክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

“ንብ ኢንተርናሽል ባንክ የነጋዴዎችና የታታሪዎች ባንክ ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ባንኩ በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ በሚል መርህ ለለውጥ የተነሳበትን አላማ በአጭር ጊዜ እያሳካ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም “ከብዙ ስኬታማ ሰዎች ጀርባ ስሙ የማይጠፋውን ንብ ባንክ ይበልጥ ከከፍታ ማማ ለማድረስ ከሌሎችም ጋር በትብብር የምናደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

 

በመግለጫው የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰን ጨምሮ የኬሮድ ልማትና ስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት እና ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከጋዜጠኛች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

15 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 4ኛው የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማው ለታዳጊ አትሌቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ህልማቸው እውን እንዲሆን ማገዝ መሆኑን አትሌት ተሰማ አብሽሮ ተናግሯል፡፡

***

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እንደ ሐገር የተጀመረውን የሬሚታንስ ካምፔይን  ምክንያት በማድረግ

Read More

You May Also like

Reports

Jobs